ቀኑ መሸ ደግሞ ነጋ
ጠዋት ሆነ ማታ መጣ
ተቆጠሩ አመታት እድሜዬም ጨመረ
ጥበቃ ፍቅርህ ግን አልተቀየረ
አለሁ ስላለኸኝ አለሁ
ኖራለው ስላለህኸኝ ቀጥላለው
አላብራራልህም ከቶ ምን እንድሻ
ታምነሀል ልትሰደኝ ወደ ህይወት እርሻ
ዳር ሆኜ ማየት ነው ስራህን ስትሰራ ከረግረግ መንጥረህ በለምለም ስትመራ
አለሁ ስላለኸኝ አለሁ
ኖራለው ስላለኸኝ ቀጥላለው
አንደበቴ ሲዘጋጅ
ቃላት ሲመርጥ ሲያበጃጅ
ተናነቀው ሲቃ
ሊያወራ ሲነሳ
አይኔ ቀድሞ አወጋ
እያወረደ እንባ
መታገስ ተስኖት
ፍቅርህን አስቦት