በሀጢያቴ ሙታን በነበርኩ ጊዜ
ህይወትን ልትሰጠኝ መጣህ ኢየሱሴ
በእኔ ፈንታ ሞተህ ህይወትን ሰጠኸኝ
የመንግስትህ ወራሽ እንድሆን አረከኝ
ጌታ ለእኔ ልዩ ነህ ለእኔ
አባ ለእኔ ልዩ ነህ ለእኔ
ኢየሱስ ለእኔ ልዩ ነህ ለእኔ
ልዩ ነህ ለእኔ
በፍቅርህ ጉልበት የራስህ አርገኸኛል
ደንዳናውን ልቤን አሸንፈኸዋል
ስለዚህ ለክብርህ ልኑር ልገዛልህ
ለውለታህ ምላሽ ምን አለ የምሰጥህ
ጌታ ለእኔ ልዩ ነህ ለእኔ
አባ ለእኔ ልዩ ነህ ለእኔ
ኢየሱስ ለእኔ ልዩ ነህ ለእኔ
ልዩ ነህ ለእኔ