ከብዙ ስቃይ
መከራ መሀል
አግኝቼሻለሁ
እወድሻለሁ
በብዙ ስቃይ
መከራ መሀል
ፈትኜሻለሁ
እወድሻለሁ
ከብዙ ስቃይ
መከራ መሀል
አግኝቼሻለሁ
እወድሻለሁ
በብዙ ስቃይ
መከራ መሀል
ፈትኜሻለሁ
እወድሻለሁ
የበኩር ፍቅር አለሜ
የልጅነት ህልሜ
የአንቺ አይነት ሴት ነበር ምጠብቀው ኖሬ
በፀባይም በውበት
ነገርሽ ታድሏል
ሀሳቤን አግኝቼ ልቤም ተደላድሏል
ሰው ነኝ ሙሉ አይደለሁ
የሚጎለኝ ብዙ ነው
ስፈልግ ነበረ ልቤን የሚሞላው
በብዙ አዛመደን
ፍቅር አቆራኝቶ
አንድ ሁኑ ብሎናል
አይለያየን ከቶ
ንፋስ መግቢያም የለው
አንዳች ቦታ ልቤ
ህይወትን አላውቃት
ያላንቺ አስቤ
በልቤ ከተማ
የኔ ባልኩት ሀገር
ነግሰሻል በመውደድ
ከብረሻል በፍቅር
ዛሬም ነገም እወድሻለሁ
ያንቺው ነኝ
ዛሬም ነገም እወድሻለሁ
ያንቺው ነኝ
ዛሬም ነገም እወድሻለሁ
ያንቺው ነኝ
ፍቅርሽ ነው ለመኖር ብርታቴ
የሆነኝ