አይጠፋም ትዝታ
ቢረሳ እንደዋዛ
ብቅ ይላል በመስኮት
የ ፀሀይ ብርሃን ይዞት
በኖርነው ልክ እንዲለካን
ትዝታችን ሆኖ ሚዛን
ላያስበልጥ አንቺን ከኔ
ያወዳድረኝ እኔን ከኔ
እኔን ከኔ
እኔን ከኔ
ትዝታችን ሆኖ ሚዛን
በኖርነው ልክ እንዲለካን
በኖርሽው ልክ የሚያውቅሽን
እስኪ አድምጪው ትዝታሽን
ትዝታሽን
ትዝታሽን
ትዝታሽን
በሐሳብ ባህር
በውቅያኖስ
በመንታ መስኮት
ነይ እንፍሰስ
ይረፍ በገላሽ
የገባው ጨረር
ትዝታው ፈረስ
ይዞን እንዲበር
አይጠፋም ትዝታ
ቢረሳ እንደዋዛ
ብቅ ይላል በመስኮት
የ ፀሀይ ብርሃን ይዞት
አይጠፋም ትዝታ
ቢረሳ እንደዋዛ
ብቅ ይላል በመስኮት
የ ፀሀይ ብርሃን ይዞት